የአብርሃም አስመላሽ ዜና እረፍት
ዓርብ፣ ጥቅምት 22 2006ማስታወቂያ
አርቲስት አብርሃም አስመላሽ ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ራድዮ የቅዳሜ መዝናኛ ዝግጅት ልዩ ልዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን አዋዝቶ በሚያቀርብበት ተወዳጅ መነባንቦቹና ጭውውቶቹ ይታወቃል ። አዲስ አበባ በልማዱ ፈረንሳይ ለጋስዮን ተወልዶ ያደገው አብርሐም በአካባቢው ለንግድ ከሚመጡ የመንዝና የወሎ ነጋዴዎች በቀሰመው የአነጋገር ዘይቤ የሚያቀርባቸው መነባንቦች የልዩ ተስጥኦው ቋሚ ምስክሮች ናቸው ። አብርሐም ለህትመት ያልበቁ በርካታ ስራዎችም ነበሩት ። ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለስራዎቹ አፍቃሪዎች ዶቼቬለ የአማርኛው ክፍል መፅናናትን ይመኛል ። እዚህ ጀርመን መጥቶ እንዲታከም እርዳታ ያስተባበሩለት የኢትዮጵያ አርቲስቶች ማህበር የጀርመን ተጠሪ አቶ ተፈሪ ፈቃደ የአብርሃምን አስከሬን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የበጎ ፈቃደኖችን አስቸኳይ እርዳታ ጠይቀዋል ። አቶ ተፈሪን በስልክ አነጋግረቸዋል ።
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ