የአሸተን ጉብኝት በሶማሊያ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 22 2004ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ ወይዘሮ ካትሪን አሸተን ትናንት የሶማሊያዋን ርዕሠ-ከተማ ሞቃዲሾን ጎብኝተዋል።ወይዘሮ አሸተን በሞቃዲሾ ቆይታቸዉ ከሶማሊያ ባለሥልጣናት፥ ከአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት አዛዦችና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።የወይዘሮ አሽተን ቃል አበይ ዛሬ እንዳስታወቁት በሶማሊያ ቋሚ መንግሥት ለመመስረት የሚደረገዉ ጥረት አበረታች ዉጤት እያሳየ ነዉ።ከሳምንት በፊት የተሰየመዉ የሶማሊያ ምክር ቤት ዛሬ አፈ-ጉባኤ መርጧል።ሥለ አሽተን ጉብኝት የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ የላከልን ዘገባ አለ።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ