በኦሮሚያ የቀጠለው ተቃዉሞ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 12 2009የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በትላንትናዉ እለት ለመንግሥት ሚድያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ «የአዋጁ መራዘም ወይም መንሳትን ጉዳይ የሚመለከተው አካል ውሳኔ ይሆናል» ሲሉ ጠቅሰዋል። አቶ ሲራጅ ለላፉት ወራቶች ሲተገበር የነበረዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአገሪቱ «ሠላም እና ፀጥታ» መማምጣት ችለዋልም ብለዋል።
መንግስት በቅርቡ የቀን ገቢ የግምት ተመን ሥራ ላይ ማዋል ከጀመረ በኋላ በኦሮሚያ ክልል በአምቦ፣ በወሊሶ፣ በፊቼ እንድሁም በሌሎች ከተሞች የትራንስፖርትና የንግድ አገልግሎት መቋረጡን ለመረዳት ተችለዋል። አምቦና ወሊሶ የነበረዉ የንግድና የትራንስፖርት አድማ ዛሬ ቀን ላይ በከፊል በነቀምት እና በቡራዩ የንግድ ተቋማትን በመዝጋት ተቃዉሞ የማሰማት አዝማሚያዎች ታይተዋል ሲሉ ኦሮሚያ መስተዳድር የመንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ አቶ አዲሱ ገልፀዉልናል።
የፖለቲካ ተንተኞችም ሆኑ አስተያየት ሰጭዎች አሁን በኦሮሚያ በግብር ጉዳይ ላይ የተነሳዉ ቅራኔና ወደ ተለየያዩ ከተሞች እየተስፋፋ ይገኛል የተባለዉ ተቃዉሞ የአዋጁን «ሠላምና ፀጥታ» ማስጠበቅ ሁኔታ ዋጋ እንዳሳጣ ነዉ የሚገልፁት። መንግስት በዚህ አኳኋን አዋጁንም ለማንሳት እንደሚቸገርም ይናገራሉ።
ትዉልድና እድገታቸዉ በምዕራብ ወለጋ ናጆ ከተማ እንደሆን ወልድ የሚምናገሩት ግን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁን ግለሰብ በቅርቡ በኦሮሚያ የተከሰተዉ ከፈተኛ ተቃዉሞን ተከትሎ ደንነቶች ሊይዙኝ ስሞክሩ ወደ ምስራቅ ሸዋ፤ ባቱ ከተማ እንደሄዱና እንደተሸሸጉ ተናግረዋል። በባቱ ከተማ ብዙ ሱቁች መዘጋታቸዉንና የማህበረሰቡ ብሶት ከግብር ዉጭ እንደሆነም ጠቅሰዋል። የባቱ ነዋሪዉ: «ከዝንብ ማር አይጠበቅም። ከዝንብ የምጠበቀዉ በሽታና ችግርን ነዉ። ከዚህ መንግስትም የሚገኘዉ እንደዛ ነዉ። በዚህ ክልል ዉስጥ ያለዉ ማህበረሰብ ከመንግስት ምንም ነገር እየጠበቀ አይደለም። ተስፋዉን ጨርሰዋል። የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ጥሩ ዉጤት አስገኝተዋል የሚሉት ለራሳቸዉ እንጅ ለሕዝቡ አደገኛ አዋጅ ነዉ።»
በኦሮምያ የተቀሰቀሰዉ ቁጣ በግብር ምክንያት ይሁን እንጅ ማህበረሰቡ በፊት ጠይቆ የነበረዉን ጥያቄ መልስ እያሻ ነዉ ሲሉ ስማቸዉን ያልጠቀሱ ሌላ ግለሰብ በዋትስአፕ ቁጥራችን ላይ የድምፅ መልክት ልከዉልናል።
አሁን በኦሮሚያ ያለዉ ሁኔታ ቅሬታ የማቅረብ ጉዳይ እንጂ ከፀጥታ ጋር የተያያዘ አይደለም የሚሉት አቶ አዲሱ አረጋ አዋጁን «ዋጋ የሚያሳጣ ጉዳይ አይደልም» ብለዋል። በአምቦ የንግድ ተሽከርካሪና የደኅነት ተሽከርካሪ ላይ የደረሰዉ ጥቃት እንዲሁም በወሊሶ የነበረዉ አለመረጋጋትን ጨምሮ ሌሎች ቦታዎች ያለዉ ተቃዉሞ አስቸካይ ግዜ አዋጁን አይፈታተንም ይላሉ።
በኦሮሚያ ያለዉ ሠላምና ፀጥታ በተሻሻለ ሁኔታ ላይ እንደምገኝ አቶ አዲሱ አረጋ ተናግረዋል። በተወሰኑ ቦታዎች የተከሰተዉን «መጠነኛ ክስተት» ወስዶ አዋጁ ይራዘማል አይራዘምም የሚል ድምዳሜ መዉሰድ ግን ያሳስታል ብለዋል።
መርጋ ዮናስ
አዜብ ታደሰ