የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለጌድኦ ዞን ተፈናቃዮች
ሰኞ፣ መጋቢት 9 2011ማስታወቂያ
በጌዲዮ ዞን ለረሀብ ለተጋለጡ ተፈናቃዮች ምግብ እየታደለ መሆኑን የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ፡፡ ባለሥልጣናቱ እንዳሉት በአሁኑወቅት ከፌደራሉ መንግሥትና ከተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች የተላኩ ተጨማሪ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታዎች ወደ አካባቢው እየደረሱ ነው፡፡ በመጠለያ ጣቢያዎቹ የሚታየውን የውሃና የጤና አገልግሎት ችግሮችን ለመቅረፍ የፌደራሉ የሚንስቴር መሥሪያቤቶች ባደረጉት ድጋፍ ከነገ ጀምሮ አቅርቦቱን ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጧል፡፡ የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ተጨማሪ ዘገባ አሰናድቷል፡፡
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ