የአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው መሰናበት
ሐሙስ፣ ጥር 29 2006ማስታወቂያ
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት ጁነዲን በሻህ ለሮይተርስ አሰልጣኝ ሰዉነት እና ምክትላቸዉ እንዲሁም የበረኛዉ አሰልጣኝ ብሄራዊ ቡድኑን ባለፉት ዓመታት አነቃቅተዉ ለታሪካዊ ስኬት ማድረሳቸዉን ገልጸዋል። ሆኖም አሁን የተጣለዉ መሠረት የተሻለ ፍሬ እንዲያሳይ በወጣቶች መገንባት ይኖርበታል ብሎ ፌዴሬሽኑ እንደሚያምን እና፤ በቅርቡም አዲስ አሰልጣኝ እንደሚሰየም አመልክተዋል። አዲሱ አሰልጣኝ ከሀገር ዉስም ሆነ ከዉጭ ሊሆን እንደሚችል ነዉ የተገመተዉ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ እንደሚሉት ፌሬዴሽኑ ያሳለፈዉን ዉሳኔ አልጠበቁትም። አቶ ሰውነትን በስልክ አነጋግረናቸዋል።
ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ