የአርትዩር ራምቦ መጽሐፍ በአማርኛ
ሐሙስ፣ ሰኔ 16 2008ማስታወቂያ
ረምቦ ሐረር ውስጥ በቆየባቸው አሥር በሚጠጉ ዓመታት ውስጥም የአፄ ምኒልክ አማካሪ ከነበረው ከስዊዛዊው አልፍሬድ ኤልግ እና ከራስ መኮንን ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንደነበረው ይወሳል። በ37 ዓመቱ ሕይወቱ ያለፈው የረምቦ የትውልድ ከተማ ሻርቪል ከሐረር ጋር በእህትማማችነት የተቆራኘች ከተማ ናት። ሐረርም የረምቦን የቀድሞ መኖሪያ ቤተ መዘክር አድርጋለች። የአርተር ራረምቦ የሥነ-ጽሁፍ ሥራዎች በበርካታ ቋንቋዎች የተተረጎሙ ቢሆንም ወደ ኣማርኛ የተመለሱት ግን በቅርቡ ነው። የዚህ እውቅ ፈረንሳዊ ደራሲ በርካታ የግጥምና የሥነ-ጽሁፍ ስብስቦች የተካተቱበት ከፈረንሳይኛ ቋንቋ ወደ አማርኛ የተተረጎመ መጽሐፍ ፓሪስ ውስጥ ባለፈው ሰሞን ተመርቋል። በምረቃው ሥነ-ስርዓት ላይ የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ተገኝታ ነበር።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ