1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአርበኝነት ዉሎና ባህላዊዉ ድርሻ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 25 2004

ከ1928 እስከ 1933 ዓ,ም ኢትዮጵያን የወወረዉን የጣልያንን ጦር ለማባረር የተካሄደው የአምስት አመት ትግል ያበቃበት በመላ ኢትዮጵያ ታስቦ ይዉላል። በየአመቱ ሚያዝያ ሃያ ሰባት ታስቦ የሚዉለዉ ይህ የአርበኞች ቀን ጥንታዊ ጀግኖች አባቶቻችን በዱር በገደሉ ተዋድቀዉ አገራችንን ከጠላት ነጻ ያደረጉበትን ገድል ለማክበር ነዉ።

https://p.dw.com/p/14o6s
ምስል DW

ከ1928 እስከ 1933 ዓ,ም ኢትዮጵያን የወወረዉን የጣልያንን ጦር ለማባረር የተካሄደው የአምስት አመት ትግል ያበቃበት ዕለት በመላ ኢትዮጵያ ታስቦ ይዉላል። በየአመቱ ሚያዝያ ሃያ ሰባት ታስቦ የሚዉለዉ ይህ የአርበኞች ቀን ጥንታዊ ጀግኖች አባቶቻችን በዱር በገደሉ ተዋድቀዉ አገራችንን ከጠላት ነጻ ያደረጉበትን ገድል ለመዘከር እና የአምስት አመት ትግል በድል የተጠናቀቀበትን ቀን ለማክበር ነዉ።

በኢትዮጵያ አርበኝነት ከባህል አንፃር ሲታይ በትግሉ ከፍተኛ የስነ-ቃል ሃብት የጀግንነት ግጥሞች የተገኙበት ዘመን እንደነበር ታዋቂ ኢትዮጵያዉያን የስነ-ጽሁፍ ሰዎች በተባ ብዕራቸዉ ያስቀመጡልን የታሪክ ማህደር ይመሰክራል። ገጣሚ እና ጋዜጠኛ አበባዉ መላኩ በዚህ ወቅት በስነ-ጽሁፍ ዘርፍ ላይ ጥሩ ጥሩ ደራሲያን ማስታወሻ በመጻፍልምዳቸዉን ያደበሩበትም ወቅት እንደ ነበር በምሳሌ ይገልጽልናል።

በአርበኝነቱ ዘመን የተወለዱ ኢትዮጵያዉያን ጻህፍት በስነ -ጽሁፍ ተለኩሰዉ የአገራቸዉ የስነ-ጽሁፍ ዋልታ ሆነዉ ተገኝተዋል። የአርበኝነቱ ስሜት ከስነቃሉ ከሽለላዉ ከቀረርቶዉ ጋር ተያይዞ በተለይ ለስነ-ጽሁፍ ትልቅ ፋናም ነበር። በዚህ በአምስት አመቱ የትግል ዘመን ለአገራቸዉ ነጻነት ከተዋደቁት የሴት አርበኞች መካከል የ112 አመት አዛዉንት እንደሆኑ የነገሩን እና የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች አርበኞች ማህበር አባል የሆኑት ወ/ሮ የሸዋ ጸሃይ ወልደጻድቅን አነጋግረናቸዋል።

የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች አርበኞች ማህበር በአምስት አመቱ ትግል ዘመን የተጋደሉ ኢትዮጵያዉያን አማካኝነት የተቋቋመ ማህበር ሲሆን፣ በአሉ በአብዛኛዉ እነዚህን አባት አርበኞች የሚጠቅስ ቢሆንም፣ እለቱ የኢትዮጵያ ነፃነት ያስገኙ የቀድሞ አባት እናቶች ድል የመላ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ድል መሆኑ እሙን ነዉ። ድሉ በተለይ በባህላችን በስነ-ቃሉ ዙርያ ላይ ድንቅ ነገር የተገኘበት ነበር።

ከነጻነት በኋላም ቢሆን በዝያዉ በአርበኞቹ ዘመን በኢትዮጵያን የነበረዉ ሁኔታ በስነ-ግጥሙ በስነ-ቃሉ በስነ-ጽሁፉ ዘርፍ የአርበኝነቱ ዉሎ ለባህል ያለዉ ድርሻ የላቀ ነበር። በአምስት አመቱ ተጋድሎ የነበረዉን ባህል፣ ታሪክ በጽሁፋቸዉ ለማንጸባረቅ የሞከሩ ምዕራባዉያን ጻህፍት በአለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ታሪክና ባህል ያንጸባረቁበትም አንዱ ምክንያት ነበር።

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

Haile Selassie
ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ሃይለስላሴምስል AP