የአረንጓዴ ጀግኖች
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 8 2000ማስታወቂያ
በአገራችን ባለፈዉ ሰሞን የአካባቢ ተቆርቋሪዎች መድረክ ያስተባበረዉ የአረንጓዴ ጀግኖች ሽልማት ተካሂዷል። ዝግጅት የታሰበዉ በ1997ዓ,ም ሲሆን በቀጣዩ ዓመት በ1998 የመጀመሪያዉ፤ ዓምና ደግሞ ሁለተኛዉ እያለ ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ ነዉ የአረንጓዴ ጀግኖች በሚል ሽልማቱ የተሰጠዉ። የተሸላማዊቹ ዋና ሃብት ዕዉቅና ማግኘታቸዉ ሲሆን ከምንም በላይ ሰዉ በለፋዉና ባደረገዉ አስተዋፅዖ መታወሱ እሱን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ያበረታታልና ይበል የሚባል ጅምር ነዉ።