የአምደኛ ርዕዮት መሸለም
ማክሰኞ፣ ግንቦት 7 2004ማስታወቂያ
በእስር ላይ የምትገኘዉ ኢትዮጵያዊቷ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ ለጋዜጠኝነት ሙያ በቁርጠኝነት መቆሟን የዓለም ሴት፥ የመገናኛ ብዙሐን ባለሙያዎች ድርጅት አስታወቀ።የድርጅቱ ምክትል ሐላፊ ኤሊዛ ሙኞዝ ድርጅታቸዉ ርዕዮትን ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር ለዘንድሮ ሽልማት የመረጠበትን ምክንያት አስታከዉ እንዳሉት ርዕዮት ለእምነቷና ለጋዜጠኝነት ክብር ስትል ያላትን ሁሉ ሰዉታለች። የሰላሳ አንድ አመቷ መምሕርትና የፍትሕ ጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ በአሸባሪነት ተወንጀላ የአስራ-አራት አመት እስራትና የሰላሳ ሺሕ ብር ቅጣት ተበይኖባት ታስራለች።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሐመድ