የአሜሪካ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር የእስያ ጉብኝት9 የካቲት 2001ሰኞ፣ የካቲት 9 2001የአሜሪካ የዉጩ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን በእስያ የሚያደርጉትን ጉብኝት ዛሬ በጃፓን ጀምረዋል።https://p.dw.com/p/GvQ7ሂላሪ ሮድሃም ክሊንተንምስል APማስታወቂያክሊንተን በሩቅ ምስራቅ ቆይታቸዉ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ያደጉባት ኢንዶኔዢያን ጨምረዉ፤ ወደደቡብ ኮሪያና ቻይናም ጎራ ይላሉ። በጉብኝታቸዉ ወቅትም ትኩረት የሳበዉን የዓለም የምጣኔ ሃብት ቀዉስና ጥንቃቄ የሚሻዉን ከሰሜን ኮርያ ጋ የተገናኘዉን የደህንነት ጉዳይ እንደሚነጋገሩበት ይጠበቃል። አሳሳቢዉ የአየር ጠባይ ለዉጥም ትልቁ አጀንዳቸዉ ነዉ።