የህግ ረቂቁን «በግፊት ማስቀረት አይቻልም»- ተሟጋቾች
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 14 2010ማስታወቂያ
የአሜሪካ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት ኤች አር 128 በሚል ስያሜ በተዘጋጀው በዚህ የህግ ረቂቅ ላይ ሊሰጥ የነበረውን ውሳኔ ማራዘሙን ተቃውሟል፡፡ የህግ ረቂቁ የ71 የምክር ቤት አባላትን ድጋፍ አግኝቷል፡፡ በኮሚቴ ደረጃ በቀረበ ወቅት በሙሉ ድምጽ ማለፉን የሚያስታውሱ አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ባለሙያ በአሜሪካ በዚህ አይነት ሁኔታ ለምክር ቤት የቀረበን የህግ ረቂቅ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ባለ ግፊት ማስጣል እንደማይችል ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡ የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ አለው፡፡
መክብብ ሸዋ
ተስፋለም ወልደየስ
አርያም ተክሌ