የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ
ረቡዕ፣ ግንቦት 6 2006ማስታወቂያ
የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በኢትዮጵያ የፖለቲካው መድረክ እንዲሰፋና የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር መንግሥታቸው ግፊት ማድረጉን እንደሚቀጥል አስታወቁ ። ምክትል ሚኒስትሯ ዛሬ በቪድዮና በድረ ገፅ ቀጥታ ስርጭት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች በሰጡት መልስ ኢትዮጵያና ግብፅ በአባይ ላይ ያላቸውን ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱም ጠይቀዋል ። የደቡብ ሱዳን መንግሥትና መንግሥት የሚወጉት ኃይሎች የራሳቸውንጥቅም ወደ ጎን በመተው ሰላም ለማውረድ እንዲጥሩም ጥሪ አስተላልፈዋል ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ