የአሜሪካ ምክር ቤት ዉሳኔና ትርጓሜዉ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 16 2014ማስታወቂያ
የዩናይትድስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያሳለፈው ውሳኔ ስለሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ የተሻለ ግንዛቤ የተንጸባረቀበት መሆኑን አንድ የሕግ ባለሙያ አስታወቁ።የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት የዉጪ ግንኙነት ኮሚቴ ባፀደቀዉ ዉሳኔ የኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይላት ዉጊያ እንዲያቆሙ፣ ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩና በጦርነቱ ለተጎዳዉ ሕዝብ የሰብአዊ ርዳታ ይደርስ ዘንድ እንዲፈቅዱ ጠይቋል።እዚያዉ አሜሪካ የሚኖሩት ዶክተር ፍፁም አቻምየለህ እንዳሉት ውሳኔዉ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ይልቅ ለኢትዮጵያ ጠቃሚና የምክር ቤቱ አባላትም የተሻለ ግንዛቤ መያዛቸዉን የሚያመላክት ነው::
ታሪኩ ኃይሉ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ