የአሜሪካን ጦር ከኢራቅ መውጣት ያሳደረው ስጋት
ዓርብ፣ ነሐሴ 14 2002ማስታወቂያ
በርካታ ኢራቃውያን የአሜሪካን ጦር ሀገራቸውን ለቆ በመውጣቱ የተቀላቀለ ስሜት ነው ያደረባቸው ። በአንድ በኩል ሀገሪቱን በኃይል የያዘው የአሜሪካን ጦር በመውጣቱ ደስተኞች ናቸው ። በሌላም በኩል የፀጥታው ሁኔታ ከቀድሞው እጅግ ይባባሳል ብለው መስጋታቸውም አልቀረም ። የዶይቼቬለው ራይነር ዞሊሽ እንደሚለው የአሜሪካን ሠራዊት ኢራቅን ለቆ ከወጣ በኃላ የኢራቅ ፀጥታ ተረጋግቶ መቀጠሉ ለብዙዎች ኢራቃውያን አስተማማኝ አይደለም ።
ራይነር ዞሊሽ ፣ ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ
ሂሩት መለሰ