የአሜሪካን የት/ቤት ሕፃናት ግድያ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 8 2005ማስታወቂያ
ሀገሪቱ ምንም እንኳን በተደጋጋሚ ይህን መሰል አደጋ የሚገጥማት መሆኑ ቢታይም ከዘመናት በፊት የፀደቀዉን ህገመንግስት ተገን በማድረግ ከ80 ሚሊዮን በላይ ግለሰቦች በየቤታቸዉ የጦር መሳሪያዎችን ገዝተዉ ማስቀመጣቸዉ ይሰማል። ሶስት መሳሪያ ይዞ ወደትምህርት ቤት በመሄድ ህፃናቱን የገደለዉ ወጣት ኋላ ራሱን ማጥፋቱ ቢነገርም መሳሪያዉን ያገኘዉ ከቤቱ እናቱ ገዝተዉ ያስቀመጡት መሆኑም ተገልጿል። በድርጊቱ የተደናገጠዉ ኅብረተሰብ በሃዘን ከመዋጡ ዉጭ ግን መሳሪያን በየግለሰቡ እጅ እንደመጫወቻ የመያዙ ጉዳይ ይታገድ ብሎ በይፋ አለመናገሩን እዚህ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርኩት ዋሽንግተን ዲሲዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ገልጾልናል።
አበበ ፈለቀ
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ