የአሜሪካንን ም/ቤት ዉሳኔን ኢትዮጵያ ተቃወመች
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 3 2010ማስታወቂያ
የአሜሪካ ኮንግረስ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ግድያዎች እንዲጣሩ የታሰሩ እንዲፈቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ እና አፋኝ የተባሉ ሕግጋት እንዲሻሩ የሚጠይቀውን «ኤች አር 128 » የተባለውን ረቂቅ ውሳኔ ማጽደቁን የኢትዮጵያ መንግሥት አጣጣለ። ዶቼ ቬለ ያነጋጋገራቸዉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በመንግስትም ሆነ በገዥዉ ፓርቲ በኩል የተለያዩ ጉዳዮች እየተሰሩ ባለበት በአሁኑ ወቅት ኤች አር 128 መጽደቁ “ወቅቱን ያልጠበቀና ያልተገባ ነው” ብለዋል። የኤች አር 128 የውሳኔ ሀሳብ ከመግለጫነት ባለፈ ሕጋዊ ትርጉምና አንዳችም ተፅእኖ እንደሌለው ተናግረዋል። አቶ መለስ ዓለም፤ መንግሥት ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር ምንም እንከን የለም የሚል አቋም የለዉም ሲሉም ተናግረዋል።
አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ