የአለም የገንዘብ ቀዉስና ድሆቹ ሐገራት
ዓርብ፣ ኅዳር 12 2001ማስታወቂያ
የድሆቹ ሐገራትን ችግር ማቃለል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚነጋገር አለም አቀፍ ጉባኤ በመጪዉ ሳምንት አርብ ዶሐ-ቀጠር ላይ ይደረጋል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጠራዉ ጉባኤ ላይ የሐገራት መሪዎች፥የገንዘብ ሚንስትሮች፥ የገንዘብ ተቋማት ሐላፊዎችና የንግድ ድርጅት ተወካዮች ይካፈላሉ።የበለፀገዉ አለም ክፍተኛ የገንዘብ ቀዉስ በገጠመዉ ባሁኑ ወቅት የሚደረገዉ ጉባኤ የድሆቹን ሐገራት ችግር ለማቃለል ሁነኛ እርምጃ መዉሰዱ ግን ብዙ አጠራጣሪ ነዉ።አብዱላሒ ታኮ ቤላ ያዘጋጀዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።