የተቃዉሞ እንቅስቃሴ እና እንድምታዉ
ዓርብ፣ ጥቅምት 4 2009ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ለወራት የዘለቀዉ የፀረ መንግሥት የተቃዉሞ እንቅስቃሴ የሰዉ ሕይወት እያጠፋና ንብረት እያወደመ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ መብትና ነጻነት የሚጠይቁትን ጭምር እያሳሰበ የመጣ ይመስላል። ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ አስተያየት ሰጭ እንደሚሉት ከሆነ ፀረ መንግሥት ተቃዉሞ ከሰላማዊነቱ አንፃር አብዛኛዉ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ ነበር። ይሁንና በተወሰኑ አካባቢዎች የደረሰዉ የንብረት ዉድመትና ማነትና ያነጣጠረዉ ጥቃት ዋናዉን የመብትና የነጻነት ጥያቄ እንዳያጠለሸዉ ያሳስባል ብለዋል። ሌላዉ አስተያየት ሰጭ በበኩላቸዉ ተቃዉሞ ወደ ንብረት ዉድመት የሄደበት ምክንያት የሕዝቡ ጥያቄ በአግባቡ ሰሚ ባለማግኘቱ ነዉ ይላሉ። አስተያየት ሰጭዉ አክለዉም በእንዲህ አይነቱ የተቃዉሞ እንቅንቅስቃሴ ላይ ከመብት ጥያቄ ዉጪ ሌላ አላማ ያላቸዉ ሊኖሩ እንደሚችሉ ገልፀዉ እነዚህን ሕዝቡ በንቃት ሊጠብቅ እንደሚገባ ተናግረውል። የፖለቲካ ተንታኙ አቶ የሱፍ ያሲን በበኩላቸዉ በሕዝቦች ትግል እንዲህ ዓይነት ነገሮች የተለመደ መሆኑን ገልፀዉ፤ የሕዝቡን የመብት ጥያቄ ለጊዜዉ ሊሸፍን እንጂ፤ ሊያቆመዉ እንደማይችል ይገልፀዋል።
ፀሐይ ጫኔ
ነጋሽ መሐመድ