ትምህርት
የንባብ ለሕይወት አውደ ርዕይ
ዓርብ፣ ሐምሌ 21 2009ማስታወቂያ
የ«ንባብ ለሕይወት» ዓውደ ርዕይ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ሲካሄድ ዘንድሮ ሦስተኛ ጊዜው ነው። ለአምስት ቀናት የሚቆየውን ዓውደ ርዕይ ማዘጋጀት የጀመረው ቢንያም ከበደ ይባላል። ቢንያም ለኢትዮጵያ «FM» ጣቢያዎች በጋዜጠኝነት ያገለገ ሲሆን፤ ካለፉት 15 ዓመታት አንስቶ ደግሞ ትኩረቱን ወደ ትላልቅ ዝግጅቶች ቀይሯል። ከነዚህ መካከል ንባብ ለሕይወት የተሰኘው ፕሮጀክት አንዱ ነው።
በአውደ ርዕዩ ላይ ራሳቸውን ከሚያስተዋውቁት መካከል ተርጓሚ ህይወት ታደሰ አንዷ ናት። በአሁኑ ወቅት የራሷን ድርሰት እየፃፈች ትገኛለች። በአውደ ርዕዩ ላይ ይዛ የምትቀርበው ደግሞ የትርጉም ሥራዋን ነው። ህይወት ከአንባቢነት ወደ ተርጓሚነት የተሸጋገረችው አንብባ የተረዳችውን ለሌሎች ለማሻፈል ስለምትሻ እንደሆነ ትናገራለች። እስካሁን የተረጎመቻቸው መጽሐፍት ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ነበሩ።
ዓውደ ርዕዩ ወጣቱ የእድሜ ክልል ላይ ቢያተኩርም ዘንድሮ ሁሉንም የእድሜ ክልል አንባብያን ያካተተ መሆኑን በንባብ ለህይወት ፕሪጀክት የመረጃ ክፍል ኃላፊ የሆነው ዬሴፍ ዳሪዎስ።ሕይወት ታደሰን ጨምሮ በርካታ ፀሀፊያን፣ ደራሲያን እና አንባቢያን በሚሳተፉበት እና ዓርብ በአዲስ አበባ በጀመረው ዓውደ ርዕይ ላይ እስከ 150 000 ሰዎች እንደሚሳተፉ አዘጋጆቹ ባለ ሙሉ ተስፋ ናቸው።
ልደት አበበ
ነጋሽ መሀመድ