1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኔ ክፍያ-ኢትዮጵያዊው ፔይፓል?

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 6 2008

በመንግስት መዋዕለ ንዋይ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት አስመዝግባለች በሚባልላት ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አቅርቦት እና የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት እጅግ ውስን መሆን ይተቻል። ይህ ለአዳዲስ የስራ ፈጣሪዎችና የስራ አሳቦች ፈተና ነው።

https://p.dw.com/p/1HOQf
Deutschland Wirtschaft Symbolbild Online Einkaufen im Internet
ምስል imago

ኢትዮጵያ እና የዓለም የንግድ ድርጅት

በድረ-ገጽ በቀላሉ እና በተሻለ ደህንነት ክፍያ ለመፈጸም ከሚያገለግሉ መካከል አንዱ የሆነው ፔይፓል በዓለም ዙሪያ 173 ሚሊዮን ደንበኞች አሉት።አፕል ፔይ፤ጉግል ዋሌትም ተመሳሳይ ግልጋሎት ያቀርባሉ። ለሽያጭና ግልጋሎት ክፍያ መፈጸም ገንዘብ መላክና መቀበል ዋንኛ ስራቸው ነው። ስድስት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ይህንንው ግልጋሎት ኢትዮጵያ ውስጥ ሊሞክሩት አቅደው ወደ ሥራ ገብተዋል። የ'ኔ ፔይ ድረ-ገጽ ግንባታ በከፊል ተጠናቆ ይፋ ሆኗል። ድረ-ገጹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ከሌሎች ስምንት የግል ባንኮች ጋር በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር ድረ-ገጹ ያትታል። የክፍያ አገልግሎቱ የኔ ፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በተባለ ተቋም የሚተዳደር ሲሆን ወደ ፊት ባለሱቅ የተሰኘ የመገበያያ ድረ-ገጽ እንደሚጀምርም ያስረዳል። ለመሆኑ የ'ኔ ፔይ እንዴት ይሰራል?

እሸቴ በቀለ

አዜብ ታደሰ