የኔቶ አባላት ልዩነት
ረቡዕ፣ ኅዳር 24 2012ማስታወቂያ
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሐገራት መሪዎች ለዓመታዊ ጉባኤ ለንደን-ብሪታንያ ዉስጥ እየመከሩ ነዉ። የ29ኙ አባል ሐገራት መሪዎች የጦር ተሻራኪ ድርጅታቸዉን አንድነትና ተልዕኮን በሚያጠናክሩበት ርዕስ ላይ ጊዜ ሰጥተዉ ይነጋገራሉ ተብሏል።ይሁንና ዩናይትድ ስቴትስ ለድርጅቱ የምታዋጣዉን ገንዘብ ለመቀነስ መወሰኗ፣ ከጉባኤዉ በፊት በፈረንሳይና በጀርመን፣ በፈረንሳይና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል የተፈጠረዉ ልዩነት መሪዎቹን ብዙ ማወዛገቡ አይቀርም።የምድራችን ግዙፍ የጦር ተሻራኪ ድርጅት ኔቶ ሰባኛ ዓመቱን እያከበረም ነዉ።የፓሪሷ ወኪላችን ኃይማኖት ጥሩነሕ ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች።
ኃይማኖት ጥሩነህ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ