የናይጀሪያው የጎሳ ብጥብጥ
ሰኞ፣ የካቲት 29 2002ማስታወቂያ
የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የዓይን ምስክሮች እንደተናገሩት ሰዎቹ የተገደሉት ክርስቲያኖች በሚያመዝኑባቸው በጆስ አቅራቢያ በሚገኙ ሶሶት መንደሮች ውስጥ ሲሆን ጥቃቱ የተፀመውም መንደሮቹን ከበው በሚኖሩ ሙስሊሞች ነው ። ይኽው ግጭት እንደተቀሰቀሰም ሆነ ከተባበሰ በኃላ አንድም ፖሊስ በአካባቢው አለመድረሱ እያነጋገረ ነው ። የበርካታ ሰዎች ህይወት ስለጠፋበት ስለዚሁ የጎሳ ግጭት ሂሩት መለሰ የዶይቼቬለ ራድዮ የሀውሳ ቋንቋ ክፍል ባልደረባ የሆነውን ጋዜጠኛ ባላ አብዲላሂ ታኮን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች ።
ሒሩት መለስ
ነጋሽ መሐመድ