የቻይናው መሪ የብሪታኒያ ጉብኝትና ተቃዉሞ
ዓርብ፣ ጥቅምት 12 2008ማስታወቂያ
የቻይናው መሪ ሺ ጂን ፒንግ የብሪታኒያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል ።ሺ ብሪታኒያን በጎበኙበት ወቅት ቻይናና ብሪታኒያ ከ30 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ የሚገመት የንግድ ስምምነቶች ተፈራርመዋል ።ጠቅላይ ሚኒስትር ሺ በ4 ቱ ቀናት የብሪታኒያ ቆይታቸው በየሄዱበት ደማቅ አቀባበል ቢደረግላቸውም የሚቃወሙዋቸውም አልጠፉም ። ዛሬ ወደ ሃገራቸው ከማቅናታቸው በፊትም ከንግዱ ማህበረሰብና ከሲቪክ ማህበራት መሪዎች ጋር ተገናኝተው ነበር ። የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን ቻይና የብሪታኒያ ተመራጭ አጋር ትሆናለች ብለዋል ።ቻይና በብሪታኒያ የኃይል ዘርፍ ትልቅ ሚና የምትጫወት ሃገር ናት ። ሃና ደምሴ ዝርዝር ዘገባ አላት ።
ሃና ደምሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ