የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢሰመኮ ላይ ያቀረቡት ተቃውሞ
እሑድ፣ መጋቢት 12 2013ማስታወቂያ
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ሰብአዊ ቀውስ ገለልተኛ ሆኖ ማጣራት መቻሉ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው አስታወቁ ። ሳልሳዊ ወያነ ትግራይ፣ የታላቋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ ባይቶና እና የትግራይ ነጻነት ፓርቲ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የማይካድራ የጅምላ ጭፍጨፋን አስመልክቶ ያወጣው ሪፖርት በተቀረው የትግራይ አካባቢ የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲፈጠር አስተዋጽዖ ነበረው ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉ በትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን በመላ ሀገሪቱ ገለልተኛ የማጣራት ስራ እየሰራሁ ነው ብሏል።
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
ታምራት ዲንሳ