1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ዓመታዊ ዘገባና ኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ኅዳር 24 2007

በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የዘንድሮው ዓመት የሙስና ሠንዘረዥ መሰረት ዴንማርክ እንደ አምናው ከሙስና ነፃ ከሚባሉት ሀገራት ተርታ በቀደምትነት ስትሰለፍ ሶማልያ ደግሞ በሙስና ከተዘፈቁት ሀገራት ከመጨረሻ 1ኛ ሆናለች። ኢትዮጵያና ሌሎች ሀገራትስ?

https://p.dw.com/p/1Dyt9
Infografik Korruptionsindex 2014 Englisch

ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ለ 20ኛ ጊዜ ዘንድሮ በዓለም ሀገራት ውስጥ ሙስና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የመረመረበትን ዘገባ አቅርቧል ። በዚሁ ምርመራ ዴንማርክ፣ ኒው ዜላንድ፣ እና ፊንላንድ ሙስና እጅግ ከማይታይባቸው ሀገራት ተርታ እንደቅደም ተከተላቸው ሲያስቀምጥ፣ ሶማሊያ፣ ሰሜን ኮርያ እና ሱዳን ደግሞ በሙስና ከተዘፈቁት ሀገራት ከመጨረሻዎቹ ሶስት ሀገራት እንደሆኑ ይፋ አድርጓል። አዲሲቷም የአፍሪቃ ሀገር ደቡብ ሱዳን ከመጨረሻዎቹ 5ኛ ሆናለች።« ብዙም የሚያስገርም አይደለም እንደ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ያሉ ሀገራት፣ ምክንያቱ ምንም ይሆን ምን ለረዥም ጊዜያት አለመረጋጋት የታየባቸው ሀገራት በመሆናቸው ከፍተኛ ሙስና ቢታይ የሚገርም አይደለም።»

ይላሉ በርሊን በሚገኘው የትራንስፓረሲ ኢንተርናሽናል ቢሮ ከሰሀራ በታች የሚገኙ ሀገራት የተቋሙ ተጠሪ ሻንታን ኡዊማና፤ ምንም እንኳን እነዚህ ሀገራት ከመጨረሻዎቹ ተርታ ቢሰለፉም በሙስና የተዘፈቁት ሀገራት እንደ ድርጅቱ በርካታ ናቸው።« በትራንስፓረንሲኢንተርናሽናልሙስና መለኪያ መሰረት ነጥባቸው ከ 50 በመቶ በታች በሆኑ ሀገራትም በሁሉም ዘርፍ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ፣ በድሆችና በአጠቃላይ በዜጎች የዕለት ከዕለት ኑሮ ላይ ጉዳት የሚያመጣ ሙስና ታይቷል። እዚህ ላይ እያወራን ያለነው በአስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ ስለሚታዩ ሙስናዎች ነው። ነገር ግን ለትላልቅ የመንግሥት ኮንትራቶች አዋጪ ዋጋ ያቀረቡበትን በመምረጥ ሳይሆን የሚሰጡትን በመምረጥ የሚፈፀም ከፍተኛ ሙስናዎችም አሉ።»

Chantal Uwimana Transparency International
በርሊን በሚገኘው የትራንስፓረሲ ኢንተርናሽናል ቢሮ ከሰሀራ በታች የሚገኙ ሀገራት የተቋሙ ተጠሪ ሻንታን ኡዊማናምስል Transparency International

በትራንስፓረንሲኢንተርናሽናልየሙስና መመዘኛ መለኪና መሰረት ከ50 በሞቶ ነጥብ በታች ከሆኑት ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ 33 ነጥብ ብቻ በማግኘት 110ኛውን ቦታ ይዛለች። ድርጅቱ ከገመገማቸው 174 ሀገራት መካከል፤ ጀርመን 79 ከመቶ በማግኘት በ12ኛ ስፍራ ስትሆን፣ ዮናይትድ ስቴትስ ደግሞ 17ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ትራንስፓረሲ ኢንተርናሽናል ምንም እንኳን ጀርመን 12 ደረጃ ላይ ብትገኝም ፤ ገንዘብ ከሚጭበረበርባቸው ሀገራት 28ኛ ደረጃ ላይ በመሰለፏ ፤ መንግሥት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲል ድርጅቱ አሳስቧል።

ሙስናን በተመለከተ ከአፍሪዋቃ መሻሻል ካሳዩት ሀገራት መካከል ኮት ዲቫር እና ማሊ ተመዝግበዋል። በሌላ በኩል ምጣኔ ሀብታቸው በፍጥነት በማደግ ላይ በሚገኙ ሐገራት የሚፈፀመው ሙስና ከመጠን በላይ እየጨመረ ሲሄድ ተስተውሏል። ካለፈው ዓመት ግምገማ ጋር ሲነፃፀር ሙስና ክፉኛ ጨምሮ ከታየባቸው ሀገራት መካከል ቻይና ፣ቱርክ እና አንጎላ በዋናነት ተጠቅሰዋል። ለመሆኑ ትራንስፓረንሲኢንተርናሽናልበየዓመቱ የሚያወጣው የሙስና መለኪና ትክክል ስለመሆኑ በምን ይገመገማል? የተቋሙ ከሰሀራ በታች የሚገኙ ሀገራት ተጠሪ ሻንታን ኡዊማና፤ መለኪያችን ያሉትን ያብራራሉ፤

Transparency International Logo

«ይህ መመዘኛ የተዘጋጀው የዓለም ባንክ፤ የዓለም ኢኮኖሚ መድረክ፤ የአፍሪካ ልማት ባንክ ከመሳሰሉ የተለያዩ ተቋማት የተገኙ መረጃዎችን በማሰባሰብ ነው። ስለዚህ ያደረግንው አዲስ ነገር ማግኘት ሳይሆን ከተለያዩ ምንጮች የተገኘ መረጃን በማጠናቀር የተደራጀ ዘገባ ማቅረብ ነው።የመረጃ ምንጮቹ ስለ መረጃ የማግኘት መብት፤ በአንድ ሃገር ስራ መስራት ምን ይመስላል?አሰራሮቹ እና ህግጋቱ ምን አይነት ናቸው?አተገባበሩስ ምን ይመስላል የሚሉ ጉዳዮችን ይገልጻሉ። ስለዚህ ጥናቱን በመስራት አዲስ ግኝት ይዘን አልመጣንም።ያለውን መረጃ በማደራጀት እና በማቅረብ ሀገሮች ከሌሎች ሃገሮች አኳያ ያሉበትን ሁኔታ እንዲመለከቱ ነው ያደረግንው።»

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ