የትምህርት ጥራት እና የመምህራን ወቀሳ
ዓርብ፣ ግንቦት 9 2005ማስታወቂያ
ከትምህርት ሚኒስቴር በገኘነው መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ የትምህርቱ ሽፉን ባለፉት 20 አመታት ከ19,5 ወደ 94 ከመቶ ከፍ ብሏል። ይሁንና ልጆች በትምህርታቸው ወደፊት ስኬታማ እንዲሆኑ መሰረታዊ የሆነ ትምህርት ከመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ጀምሮ ማግኘት አለባቸው።
የትምህርት ጥራት ወላጅ፣ተማሪ እና አስተማሪዎችን በአሁኑ ጊዜ እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ነው። አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን በተመለከተ ችግር መኖሩን እና የትምህርት ሚኒስቴርም ችግሩን ለመፍታት በስራ ላይ እንደሚገኝ፤ በፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ረዲ ሽፋ ገልፀዋል።በሌላ በኩል በኢትዮጵያ በአንዳንድ በገጠሩ አካባቢ የሚኖሩ መምህራን ከፍተኛ የትምህርት ጥራት ጉድለት እንዳለ ይወቅሳሉ። ለመሆኑ በትምህርት ጥራት ላይ አሉ የሚባሉት ችግሮች የትኞቹ ናቸው?በዚህ ጉዳይ ላይ የተደረገውን የወጣቶች አለም ዝግጅት ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ