የትመጣዉ ያልተረጋገጠዉ ተህዋሲ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 30 2003ማስታወቂያ
ተህዋሲዉ ከሁለት ሺ በላይ ሰዎችን በአዉሮጳ ለህመም መዳረጉ ቢነገርም መነሻ ምንጩ የት እንደሆነ አለመገኘቱ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከፍ አድርጎታል። 27 አባላት ያሉት የአዉሮጳዉ ኅብረት ሉቅሰምበርግ ላይ ዛሬ አስቸኳይና ልዩ ጉባኤ እንያካሄደ ነዉ። የአዉሮጳ ኅብረት ባለስልጣናት ተህዋሲዉ በሰዎች ህይወትና ጤና ላይ ያደረሰዉን ጉዳት ለመግታት ብቻ ሳይሆን በአትክልት አምራቾች ተግባር ላይ የጋረጠዉን እንቅፋትም አስመልክተዉ መነጋገር ይዘዋል።
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ