የታደሰ እንግዳው ኅልፈትና ዶይቸ ቨለ፣
ሰኞ፣ ሐምሌ 9 2004ማስታወቂያ
እንግዳው፤ ትናንት እሁድ፣ ከአዋሳ ወደ አዲስ አበባ ከ 2 ወንድሞቹ ጋር በመመለስ ላይ ሳለ፤ ከዜና ምንጮቻችን እንዳረጋገጥነው፣ ባጋጠመ የመኪና አደጋ ሳቢያ ፤ እርሱና፤ አንደኛው ወንድሙ ህይወታቸው አልፏል። በዚህ ዘግናኝ ህልፈተ ህይወት፣ ቤተሰብ ፤ ቤተዘመድ ፤ ጓደኞች ፣ እኛም የሥራ ባልደረቦቹ እጅግ አዝነናል። ስለሆነም የዛሬውን ሥርጭታችንን፣ ከሞላ ጎደል በአጠቃላይ፤ ለእርሱ መታሰቢያ እንዲሆን አድረገናል። በዚህ በራዲዮ ጣቢያው ማዕከል ከሚገኙ 6 ባልደረቦቹ ጋር የተካሄደው ልዩ ውይይት ፤ ቀጥሎ ይቀርባል።
ባልደረቦቹ