የታይላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሥንብትና ተቃዋሚዎች
ማክሰኞ፣ ኅዳር 23 2001ማስታወቂያ
የታይላድ ጠቅላይ ሚንስትር ሶምቻይ ዎንግሳዋት የሐገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሥልጣን እንዲለቁ ያሳለፈባቸዉን ብይን ተቀበሉት።ፍርድ ቤቱ በምርጫ ማጭበርበር የተወነጀለዉ የጠቅላይ ሚንስትር ሶምቻይ የፖለቲካ ማሕበር እንዲታገድም በይኗል።የጠቅላይ ሚንስትር ሶምቻይ መንግሥት ሥልጣን እንዲለቅ ለማስገደድ ላለፈዉ አንድ ወር ሕዝባዊ ሠልፍ እና እና አድማ ሲያደራጅ የነበረዉ ተቃዋሚ ፓርቲ የፍርድ ቤቱን ብይን በደስታ ነዉ የተቀበለዉ።ነጋሽ መሐመድ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።