የታቸር ቀብር
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 9 2005ማስታወቂያ
ባለፈዉ ሳምንት ያረፉት የቀድሞዋ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ማርጋሬት ታቸር ዛሬ ተቀበሩ። በሥንብቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ የብሪታንያዋን ንግሥት ጨምሮ የአንድ መቶ ሰባ ሐገራት መሪዎች፥ ሚንስትሮች፥ ባለሥልጣናትና በብዙ ሺሕ የሚቆጠር የብሪታንያ ሕዝብ ተገኝቷል።ብሪታንያ ዉስጥ ከቀድሞዋ የሐገሪቱ ልዕት ዳያና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ወዲሕ በርካታ ሕዝብ ለሥንብት ሲወጣ የዛሬዉ የመጀሪያዉ ነዉ።ይሁንና ታቸርን የሚቃወሙ ሰዎችም አስከሬኑ ለሥንብት በተቀመጥበት አካባቢ ተሰልፈዉ ሟቿን ፖለቲከኛ ሲያወግዙ ነበር።የሥንብትና የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ እንዳይታጎል የብሪታን ፀጥታ አስከባሪዎች የለደን ከተማ በጥብቅ ሲቆጣጠሩ ነዉ የዋሉት።ታቸር በኑዛዛቸዉ መሠረት አስከሬናቸዉ ተቃጥሎ አመዱ ነዉ-የሚቀበረዉ።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።
ድልነሳ ጌታነህ
ነጋሽ መሐመድ
ሂሩት መለሰ