እነ እስክንድር ወደ ጠባብ ክፍል ተዛውረዋል።
ዓርብ፣ መጋቢት 21 2010ማስታወቂያ
ባለፈው እሁድ ኮማንድ ፖስት ካሰራቸው ጋዜጠኞች ፖለቲከኞች እና ብሎገሮች አንዱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሞ ዛሬ ዘውዲቱ ሆሲፒታል ለህክምና መወሰዱን ወንድሙ ተናገሩ። ወንድሙ እንዳሉት ተመስገን ወደ ሆስፒታል የተወሰደው የጀርባ እና የወገብ ህመሙ ስለጠናበት ነው። ባለፈው እሁድ በተመስገን ደሳለኝ መኖሪያ ቤት ከእስር ለተፈቱ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ከተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ተይዘው የታሰሩት 11 ሰዎች የሚገኙበት ቦታ ለጤናቸው አስጊ መሆኑን የተመስገን ወንድም ለዶቼቬለ ገልጸዋል። እርሳቸው እንዳሉት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ የሚገኙባቸው እነዚሁ እስረኞች ቀድሞ ተይዘውበት ወደ ነበረው ብዙ ሰዎች ወደሚገኙበት ጠባብ ክፍል ተዛውረዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ