1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታላቁ ኮከብ ድምጻዊ ፣ የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ የቀብር ሥነ ሥርዓት መከናወን፣

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 15 2001

ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ህዝባዊ ቅርስ ሆኖ የኖረውን ታላቅ ኮከብ የኪነ ጥበብ ሰው ፣ ለመጨረሻ ጊዜ እስከወዲያኛው ተሰናብተዋል።

https://p.dw.com/p/Hcst
ዝነኛው ኮከብ አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ሥርዓተ-ቀብሩ የተፈጸመበት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣
ዝነኛው ኮከብ አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ሥርዓተ-ቀብሩ የተፈመጸበት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ምስል AP

በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን፣ በአውሮፓ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በሰሜን አሜሪካ፣ በአውስትሬሊያና በተለያዩ የአፍሪቃ አገሮች ባጠቃላይ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፣ በዝነኛው ድምጻዊ በአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ተደናግጠው በኀዘን ስሜት ተውጠው ነው የሰነበቱት። ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ የከተማይቱ ህዝብ አደባባይ በመውጣት ኀዘኑን በመግለጽ ነፍስ ይማር! ሲል ውሏል። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቀብሩን ሥነ-ሥርዓት፣ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ለመከታተል ችለዋል። ስለዝነኛው አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ሥርዓተ-ቀብር ታደሰ እንግዳው የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

TE/TY/AA