የታላላቅ ሐይቆች ሃገራት ትብብር
ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 2007ማስታወቂያ
ግጭቶች የሚፈራረቁባቸው የታላላቅ ሐይቆች አካባቢ ሃገራት በልማትና በምጣኔ ሃብት ትስስር ላይ እንዲያተኩሩ ተጠየቁ ። ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ የሃገራቱ ውሳኔ ሰጭ አካላት የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎችና ባለሃብቶች ባካሄዱት ምክክር በካባቢው ችግሮች ወደ ግጭት እንዳያመሩ ሃገራቱ ለልማትና ለመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል ። ከሃገራቱ አንዳንዶቹ ባለፉት 10 ዓመታት የማይናቁ የኤኮኖሚ እድገቶች ማስመዝገባቸውና የያዙት አቅጣጫም የሚያበረታታ መሆኑ ተገልጿል ። ዝርስሩን የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ