የቱርክ ምርጫ ዉጤት እና ከአዉሮጳ ጋር ያላት ግንኙነቷ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2007ማስታወቂያ
ፕሬዝደንት ራሲፕ ጣሂብ ኤርዶኻን በጎርጎሪዮሳዊዉ 2002ዓ,ም ፓርቲዉን ከመሠረቱ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ወቅቶች እስከ2014ምርጫ ድረስ የሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር በመሆን ቱርክን መርተዋል። በአሁኑ ምርጫ ፓርቲያቸዉ ከጠቅላላዉ 550 የምክር ቤት መቀመጫ ሁለት ሶስተኛዉን ቢያገኝ ኖሮ ሀገሪቱን ለፕሬዝደንቱ ይበልጥ ስልጣን ለሚሰጠዉ ወደፕሬዝደንታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመቀየር እቅድ ነበራቸዉ። ምርጫዉ ዓለም አቀፍ መስፈርትን ያሟላ እንደነበር ቢነገርለትም ቱርክን ከአዉሮጳ ኅብረት ለመቀላቀል የሚያበቃት አይመስልም።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ