የቱርክና የሶርያ ፍጥጫና ግጭት24 መስከረም 2005ሐሙስ፣ መስከረም 24 2005ትናንት ከሶርያ ምድር በተወነጨፈ ሞርታር አምስት ዜጎቿ የተገደሉባት ቱርክ የአፀፋ ጥቃት ሰነዘረች። በሁለቱ ተጎራባች ሀገሮች መካከል የተካረረዉ ፍጥጫ እንዲረግብ የአዉሮጳ ኅብረት ሲያሳስብ፤ የሰሜን አትላንቲ የጦር ቃል ኪዳን ኔቶ በበኩሉ የሶርያን ርምጃ አዉግዟል።https://p.dw.com/p/16JoLምስል Reutersማስታወቂያ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመግለፅም የተመድ የፀጥታዉ ምክር ቤትና ኔቶ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂደዉ መግለጫ አዉጥተዋል። ቱርክ በኔቶ አባልነቷ የተባባሪ ሀገሮችን ድጋፍ ስትጠይቅ የሀገሪቱ መንግስትም እንዲሁ ሶርያ ላይ ወታደራዊ ርምጃ ለመዉሰድ በሚያስችለዉ ሁኔታ ላይ እየመከረ ነዉ። ሸዋዬ ለገሰ አርያም ተክሌ