1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተፈጥሮ ከባቢ አየር መለዋወጥና ስጋቱ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 30 1999

በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ፣ 12ኛዉ የተባበሩት መንግስታት የአየር ጥበቃ ጉባኤ በኬንያ መዲና ናይሮቢ ተጀምሮአል

https://p.dw.com/p/E0hk
በኬንያ የአየር ጥበቃ ጉባኤ
በኬንያ የአየር ጥበቃ ጉባኤምስል AP

ይህ ሁለት ሳምንት የሚቆየዉ ጉባኤ፣ ስድስት ሺህ ያህል የተለያዩ ተመራማሪዎችን፣ የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅት ተወካዮች፣ እንዲሁም፣ በአየር ጥበቃ ዙርያ ያሉ ፖለቲከኞችን ሲያሳትፍ ልዑካኑ እየጨመረ የሄደዉን የከባቢ አየር ሙቀት መጠን ይዞታ ላይ ዉይይታቸዉን ቀጥለዋል። ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ደቡብ ኒጀርና፣ ቻድ እንዲሁም አብዛኛዉ የኢትዮየዽያ ግዛቶች ለችግሩ ከተጋለጡት አገሮች ግምባር ቀደሞቹ ናቸዉ። የከባቢ አየር መበከል እና መቀየር በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ገበሪዎች ላይ ያስከተለዉን ችግር የዶቼ ቬለዋ Dagmar Wittek ዘግባለች።

የደቡብ አፍሪቃዉ ገበሪ፣ አቶ ሪሽተር ዮርዳን በደቡብ አፍሪቃዊቷ ፍሪ ስቴት ገጠር የ 250 ቀንድ ከብቶች ጌታ ናቸዉ። ታድያ ከዚህ የቀንድ ከብቶቻቸዉ መካከል 40 ያህሉ ብቻ ጥሩ የሆነ የድልብ እና የኮርማ ከብት አቋም የሚታይባቸዉ ሲሆኑ ። አቶ ሪሽተር የኮርማ ከብት ለማርባት በመኖ እጦት ምክንያት ችግር መምጣቱን ይናገራሉ። ለግጦሽ የሚሆን ሚዳ የለም ፣ ሳሮች እና አትክልቶች ደርቀዉዋል ሜዳዎች ወደ ድንጋያማነት ተቀይረዋል ባይ ናቸዉ
«በየግዜዉ የአየሩ ጸባይ ቃጠሎ እና በጣም ደረቃማ ሆንዋል። ካለፉት ጥቂት አመታት ጀምሮ ዝናቡም ወቅቱን ጠብቆ አይመጣም። እንደ አመቱ ወራት ቢሆን በመስከረም ነበር ዝናብ የሚጀምረዉ። አሁን እንደምታዩት እኛ ጋር ህዳር ገብቷል ዝናብ ጠብ ብሎ አያዉቅም
እዚህ ላይ አቶ ሪሽተር፣ በአካባብያቸዉ፣ በርግጥም የአየር ጸባይ መቀያየር፣ እንደተከሰተ እና፣ ለወደፊቱም ሁኔታዉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን ለጠቆም ነዉ የፈለጉት። በአየሩ መለዋወጥ ሳብያ፣ እኚሁ ገበሪ፣ ለወደፊቱ ማርባት የሚፈልጉት የጋማም ሆነ የቀንድ ከብት ሃሩርን መቋቋም የሚችል፣ ጥቂት የግጦሽ ሳር የሚያስፈልገዉ አይነቱን እንደሚፈልጉ ነዉ የገለጹት። እንደነዚህ አይነቶቹ ከብቶች በቆዳቸዉ ላይ በጣም ጥቂት እና የሚያብረቀረቅ አይነት ጸጉር የለበሱ ሲሆን፣ ዳልቻ እና ቡላ አይነት መሆን አለበትም ባይ ናቸዉ። በአየር መዛባት ምክንያት፣ የአቶ ሪሽተር የከብት እርባታ፣ ከአመት ወደ አመት ዉጤት አልባ እየሆነ በመምጣቱ እና ለዘር የሚሆን የኮርማ ከብትም በመጥፋቱ በሰዉ ሰራሹ ማራብያ ለችግሩ ማለፍያ የሆነ መልስ እንደሆነ ያምኑበታል። የአቶ ሸሪፍ ባለቤት በአካቢያቸዉ ስላሉ ገበሪዎች ለዝናቡ መጣል ጸሎት በማድረስ በተስፋ ላይ ናቸዉ ይላሉ። ነገር ግን በዚህ አካባቢ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ከዘነበ ትልቅ ዱብዳ ነዉ!
«ገበሪዎች፣ በአመት ዉስጥ፣ ጠንቅቀዉ የሚያዉቁት፣ የቡቃያ ወራቶች አሉን፥ ነገርግን በአሁኑ ወቅት ዝናቡ በጣም ዘግይቶ ሊዘንብ ስለሚችል፣ ቡቃያዉን በወቅቱ የማግኘቱ እድል በጣም የመነመነ ነዉ። ያ ማለት ደግሞ ምናልባት ታህሳስ ላይ ቡቃያ ልናገኝ እንችላለን፣ ነገር ግን መጋቢት ላይ ብርዳማዉ ወቅት ይጀምራል፣ ስለዚህም ምርት የመሰብሰብያዉ ግዜ ያልፋል ወይም ተዛብቶአል።

ባለፉት 30 አመታት በደቡብ አፍሪቃ የእርሻ ማሳም ሆነ የተክል ስፍራ በአየር መለዋወጥ ሳብያ በእጥፍ ደረቃማ እና ምድረ በዳማ ሆነዋል። እንደ አየር ጥበቃ ተመራማሪዎች እና ተንታኞችም የዛሪ 45 ግድም ይከሰታል የሚባለዉ የአየር ቀዉስ፣ እንደ ደቡብ አፍሪቃ ባሉ አገሮች፣ የቀዉሱ መከሰት፣ ያን ያህል አመት አይጠብቅም ነዉ ፍራቻዉ!