የተጠርጣሪ ሽብርተኞች ስቃይ አጣሪ ኮሚሽን30 ሰኔ 2002ረቡዕ፣ ሰኔ 30 2002የእንግሊዝ የስለላ ድርጅቶች የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸውንና በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች በፓኪስታንና በጓንታናሞ እስርቤቶች በነበሩበት ጊዜ ግርፋትና ድብደባ ሲደርስባቸው ወይ በተባባሪነት አልያም በቸለተኝነት ጉዳዩን ማለፋቸው ተገቢ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ክስ ይቀርባል።https://p.dw.com/p/ODBLብንያም ሞሀመድምስል APማስታወቂያበተለይም በትውልድ ኢትዮዽያዊ በሆነው በቢንያም መሃመድ ላይ የደረሰው ስቃይ የብዙዎችን የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ተቃውሞ አስነስቷል። ይህን በእዚህ እንዳለ ጉዳዩን የሚያጣራ ኮሚሽን እንዲቋቋም ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ትላንት አስታውቀዋል። የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳው ጌታነህ ዘገባ አለው። ድልነሳው ጌታነህ ፣ መሳይ መኮንን ሂሩት መለሰ