የተከሰከሰዉ የኢትዮጵያ አዉሮፕላን የምርመራ ዉጤት
ሐሙስ፣ መስከረም 4 2004ማስታወቂያ
ከአንድ አመት ከመንፈቅ በፊት ሊባኖስ ርዕሠ-ከተማ ቤይሩት አጠገብ ወድቆ ሥለተከሰከሰዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላንን የአደጋ መንስኤ ሲደረግ የነበረዉ ምርመራ ተጠናቅቋል። የምርመራዉ ዉጤት የአደጋዉ መንስኤ የአብራሪዉ ሥሕተት ነዉ ወደሚለዉ ድምዳሜ ያዘነበለ መስሏል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን መርማሪዎች መረጃዎቼን አላካተቱም በማለት ዉጤቱን አልተቀበለዉም።ወደ ቤይሩት ተጉዞ የነበረዉ የአየር መንገዱ የመልዕክተኞች ጓድም የመርማዎቹን ሥብሰባ አቋርጦ ወደ ሐገሩ ተመልሷል።በአደጋዉ አዉሮፕላኑ አሳፍሯቸዉ የነበሩ ዘጠና መንገደኞችና ሠራተኞች በሙሉ ሞተዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ሂሩት መለሰ