1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተከሰሱት መፅሄቶችና ጋዜጣ እንዲሁም የጋዜጠኞቹ ስደት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 7 2006

ባለፈው ቅዳሜ በአንባብያን ይጠበቁ የነበሩ ሦስት መፅሄቶችና አንድ ጋዜጣ ሳይታተሙ ቀርተዋል ። ያልታተሙት መፅሄቶችና ጋዜጣ የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ክስ እንደመሠረተባቸው ካስታወቀው አምሥት መፅሄቶችና ጋዜጣ መካከል ናቸው ።

https://p.dw.com/p/1CtiN
Zeitungen Äthiopien
ምስል DW

የፍትህ ሚኒስቴር ለአምሥቱ መፅሄቶችና አንድ ጋዜጣ አሳታሚዎች የክስ መጥሪያ አቅርቧል ። በዚህም መሠረት ከነገ በስተያ ነሐሴ ዘጠኝ፣ ቀን 2006 ዓም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ።ከተከሠሡት መካከል የአዲስ ጉዳይ መፅሄት ባለቤትና አሳታሚ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር አገር ለቀው መውጣታቸው ተሰምቷል ። ክስ ከተመሰረተባቸው መካከል የእንቁ ሳምንታዊ መጽሄት ዋና አዘጋጅ አቶ ፍቃዱ ማህተመወርቅ ላለመታተማቸው ምክንያቱን እንደሚከተለው ያስረዳሉ።

እንቁ መጽሄትን ያትም የነበረው የፋኖስ ማተሚያ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ድርጅታቸው ሳምንታዊውን መጽሄት አለማተን አምነው ምክንያቱን እንደሚከተለው ያስረዳሉ።

Symbolbild Hammer im Gerichtssaal
ምስል picture-alliance/ dpa

የፍትህ ሚኒስቴር የክስ ወረቀት ደርሶናል የሚሉት የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ግዛው ታዬ የጋዜጣቸው መከሰስ በስራ ባልደረቦቻቸው ዘንድ አለመረጋጋት መፍጠሩን ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬን ጨምሮ ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ፣ ከፍተኛ አዘጋጅ ጋዜጠኛ እንዳለ ተሽ እና አዘጋጅና አምደኛ ሀብታሙ ስዩም ሀገር ጥለው ለመሰደድ መገደዳቸው ተሰምቷል።የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬና ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ ከሃገር ለመውጣት ያስገደዳቸውን ሁኔታ እንደሚከተለው ያብራራሉ።

መርጋ ዮናስ

ተክሌ የኋላ