ፈረንሳይ ከአፍሪካ 3ሺህ ስደተኞችን ለመቀበል ተስማማታለች
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 17 2010ማስታወቂያ
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሊቢያ ከደረሱ በኋላ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኙ ከነበሩ አፍሪካውያን ስደተኞች መካከል የተወሰኑትን ኒጀር እና ቻድ ወዳሉ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች እያዛወረ ነዉ፡፡ ፈረንሳይ በእነዚህ ጣቢያዎች ከሚገኙት መካከል ሶስት ሺህ ስደተኞችን እስከ ጎርጎሮሳዊው 2019 ዓ.ም. ድረስ እንደምትቀበል አስታዉቃለች። የመጀመሪያዎቹን 55 ስደተኞች ባለፈው ሳምንት ፈረንሳይ ደርሰዋል፡፡
ፈረንሳይ “ስደተኞችን እየተቀበልኩ ነው” ብትልም በስደተኞች አያያዟ ተደጋጋሚ ትችቶች ይቀርብባታል። ሀገሪቱ አዲስ ስደተኞችን እና ተገን ጠያቂዎችን በተመለከተ ያዘጋጀችው ረቂቅ ሕግም ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ረቂቅ ህጉ በሀገሪቱ ምክር ቤት ለውይይት ከመቅረቡ በፊት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና እርዳታ ሰጪ ተቋማት “የስደተኞችን መብት የሚገፋ እና ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያስገድድ ነው” በሚል ነቅፈዉታል። የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ የላከቸውን ዝርዝር ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ነጋሽ መሐመድ