የተባባሰው የዩክሬን ቀውስ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 13 2006ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንት ጄኔቫ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ሩስያ ዩክሬን አሜሪካንና የአውሮፓ ህብረት የደረሱበት ስምምነት የዩክሬንን ውጥረትያረግባል ተብሎ የተጣለበት ተስፋ እየደበዘዘ ሄዷል ። ስምምነቱ ምሥራቅ ዩክሬን ውስጥ በኃይል የተያዙት የመንግሥት ህንፃዎች እንዲለቀቁ መሣሪያ የታጠቁም ትጥቃቸውን እንዲፈቱ የሚጠይቅ ቢሆንም ይህ እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም ። ለችግሩ መባባስ ምዕራቡ ዓለም ተጠያቂ የሚያደርጋት ሩስያ በኬቭ መንግሥት ላይ ወቀሳዋን አጠናክራለች ። ሩስያ የዩክሬን መንግሥት መገንጠል ከዩክሬን እንገንጠል በሚሉ ኃይሎች ላይ ፣ያለፈው ሳምንቱን ስምምነት በመጣስ ኃይል እየተጠቀመች ነው ስትል እየከሰሰች ነው ። በዚህ መካከል የዩናይትድ ስቴትሱ ምክትል ፕሬዝዳንት ጆባይደንዛሬኬቭገብተዋል ስለ ዩክሬን ወቅታዊ ሁኔታ የበርሊኑን ወኪላችንን ይላማ ኃይለ ሚካኤልን ስቱ ድዮ ከመግባቱቴ በፊት በስልክ አነጋግሬው ነበር ።
ይልማኃይለሚካኤል
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ