የተቃዉሞ ሠልፍ በለንደን
ዓርብ፣ መስከረም 3 2006ማስታወቂያ
ብሪታንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የኦሮሞ ተወላጆች የኢትዮጵያ መንግሥት በሐገሪቱ ሕዝብ በተለይም በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ይፈፅመዋል ያሉት የሠብአዊ መብት ረገጣ እንዲያቆም በሠላማዊ ሠልፍ ጠየቁ።ዛሬ ለንደን ብሪታንያ ምክር ቤት ፊትለፊት የተሠለፉት የኦሮሞ ተወላጆች እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰዉ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነዉ።የብሪታንያ መንግሥት ሠልፈኞቹ «ዜጎቹን ይበድላል» ላሉት ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሠጠዉን ድጋፍ እንዲያቆም ሠልፈኞቹ ጠይቀዋል።ጥያቄያቸዉን ለብሪታያ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በደብዳቤ ማመልከታቸዉንም አስታዉቀዋል።የለንደንዋ ወኪላችን ሐና ደምሴ ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች።
ሐና ደምሴ
ነጋሽ መሐመድ