የተሳካው የቺሌው ህይወት የማዳን ዕርምጃ4 ጥቅምት 2003ሐሙስ፣ ጥቅምት 4 2003ለ 69 ቀናት በማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ውስጥ ተቀብረው የቆዩትን 33 የቺሊ የማዕድን ሠራተኞች የማውጣቱ ስራ ያለ አንዳች እንከን ተጠናቋል ።https://p.dw.com/p/PeFdምስል APማስታወቂያየማዕድን ሰራተኞቹን ተራ በተራ በሚሳኤል መሰል ቱቦ ወደ መሬት የማውጣት የረቀቀ ተግባር በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን አስደምሟል ። የልብ አንጠልጣዩ ሂደት ውጤት ቺሊያውያንን እጅግ አስፈንድቋል ። ፕሬዝዳንታቸውን አኩርቷል ። ከማዕድን ሰራተኞቹ አብዛኛዎቹ በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል ። ሂሩት መለሰ ተክሌ የኋላ