የተራቀቀው የሳውዲ አረቢያ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርስቲ
ማክሰኞ፣ መስከረም 19 2002ማስታወቂያ
በሀገሪቱ ንጉስ አብዱላ የተሰየመው ይኽው ዩኒቨርስቲ ከተለያዩ ሐገራት የተውጣጡ 70 ፕሮፌሰሮች ያሉት ሲሆን ከ 61 አገራት የመጡ 800 የውጭ ሀገር ተማሪዎችንም ተቀብሏል ። ከዩኒቨርስቲው ዋነኛ ዓላማዎች አንድ የሳውዲ አረቢያ ሳይንቲስቶችን ማፍራት ቢሆንም አሁን የመማር ዕድሉን ያገኙት የሳውዲ አረቢያ ዜጎች ግን አስራ አምስት በመቶው ብቻ ናቸው ። ዩኒቨርስቲው ከሌሌች የሳውዲ አረቢያ ዩኒቨርስቲዎች በተለየ ሴቶችና ወንዶች በአንድ ላይ የሚማሩበት በመሆኑም ይለያል ። ነብዩ ሲራክ ከጀዳ ዝርዝሩን ልኮልናል
ነብዩ ሲራክ ፣ ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ