የተ.መ. የሰብዓዊ መብቶች ምክርቤት እና ጀርመን
ሰኞ፣ ጥር 25 2001ማስታወቂያ
ለሁሉት ሳምንታት በሚቆየው በዚሁ ግምገማ ላይ የሚካፈሉት የጀርመን መንግስት ልዑካን የተደባለቀ ስሜት ይዘው ነው ወደ ስብሰባው ያቀኑት ። ጀርመን ዲሞክራሲያዊት አገር እንደመሆንዋ መጠን በህገ መንግስትዋ የሰብዓዊ መብት ጥበቃን በማስፈሯ በግምገማው ሰብዓዊ መብት ጣሽ ናት ተብላ ስለማትወገዝ አያሰጋቸውም ። ሆኖም ታዳጊ ሀገራት ከሚያመዝኑበት ምክርቤት በጀርመን የውጭ መርህ ላይ አትኩረው ለሚነሱ በርካታ አስጨናቂ ጥያቄዎች የጀርመን ልኡካን መዘጋጀት ይኖርባቸዋል ።