የተመ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር የኢትዮጵያ ጉብኝት
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 25 2009ማስታወቂያ
ጉብኝታቸዉን አስመልክቶ የተቋሙ ቃል አቀባይ ለዶይቼ ቬለ እንዳስታወቁት ባለስልጣኑ የተቃዋሚ መሪዎችንና የመንግሥት ባለስልጣናትን አግኝተዉ ያነጋግራሉ። የዚህን ጉብኝት አላማ አስመልክቶ ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የሰብዓዊ መብትና የዓለም አቀፍ መብት መምህር በበኩላቸዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት፤ ተጠያቂነትን ለማስፈን በራሳችን መንገድ አጥርተን የሞተዉን ሰዉ ቁጥር ዘገባ አቅርበናል ለዘገባችን እዉቅና ስጡልን ለማለት ያሰቡበት ግብዣ ነዉ ይላሉ። ዝርዝሩን የዋሽንገተኑ ወኪላችን ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ