የቦልቲሞሩ ረብሻና ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን23 ሚያዝያ 2007ዓርብ፣ ሚያዝያ 23 2007በምሥራቂዊ ዩናይትድ ስቴትስዋ ፌደራዊ ክፍለ ሃገር በሜሪላንድ ዋና ከተማ በቦልቲሞር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሳለ በደረሰበት የአካል ጉዳት ሰበብ ሳይሞት እንዳልቀረ ከተነገረው አፍሪቃዊ አሜሪካዊ ፍሪድሪክ ግሬይ ቀብር በኋላ በተቀሰቀሰው ሁከት በርካታ ንብረት አውድሟል።https://p.dw.com/p/1FIrrምስል Getty Images/K. Betancurማስታወቂያ አንዳንድ የንግድ ድርጅቶችም ዝርፊያ ተካሂዶባቸዋል። በግርግሩ ምክንያት በከተማይቱ የንግድ እንቅስቃሴም ቀዝቅዟል። በአሁኑ ጊዜ ከተማዋ በምን ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን ቦልቲሞር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያንና ኤርትራውያን አሜሪካውያንን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ። መክብ ሸዋ ኂሩት መለሰ ሸዋዬ ለገሰ