የብራና መፅሐፍት ተያዙ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 1 2010ማስታወቂያ
የተለያዩ የብራና መፅሐፍትን ከኢትዮጵያ ለማስወጣት የሞከሩ አንድ ቻይናዊ እና ተባባሪዎቹ ተይዘዉ በፍርድ ቤት መቀጣታቸዉን የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።ሰዎቹ የተያዙት አንድ መቶ ያክል ታሪካዊ የብራና መፅሐፍትን ወደ ዉጪ ለማስወጣት ሲሞክሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ጣቢያ ነዉ።የተያዙት መፅሐፍት ለባለሥልጣኑ ተሰጥተዋል።ይሁንና በሰዎቹ ላይ ሥለተጣለዉ ቅጣትም ሆነ ሥለተያዙበት ቀን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን የጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዘገባ የጠቀሰዉ ነገር የለም።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ