የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር የደቡብ አፍሪቃ ጉብኝት23 ግንቦት 1999ሐሙስ፣ ግንቦት 23 1999የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌር በዚሁ ሥልጣናቸው ሰሞኑን በአፍሪቃ በጀመሩት የመጨረሻ ጉዞዋቸው ዛሬ ጆሀንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ገቡ። ብሪታንያዊው ጠቅላይ ሚንስትር ቀደም ባሉት ቀናት ሊቢያን እና ሲየራ ልዮንን ጎብኝተዋል። ብሌር ሁለት ቀናት በሚቆዩባት ደቡብ አፍሪቃ በጆሀንስበርግ የንግድ ዩኒቨርሲቲ ሰፋ ያለ ዲስኩር አሰምተዋል። የብሌርን ንግግር ያዳመጠውን የብሪታንያውያኑን ዕለታዊ ሱንደይ ታምስ ጋዜጠኛን አርያም ተክሌ በስልክ አነጋግራዋለችhttps://p.dw.com/p/E0b0ቶኒ ብሌርምስል APማስታወቂያ።