የብሪታንያ ሳይንቲስቶችና መካንነት
ሐሙስ፣ ነሐሴ 7 2001ማስታወቂያ
የብሪታንያ ሳይንቲስቶች የወንዶችን የመካንነት ችግር ሊያስወገድ የሚችል ብልሐት አገኘት አሉ።ኒዊ ካሲል-ብሪታንያ የሚገኙ ሳይንቲስቶች ሰሞኑን እንዳስታወቁት የሰዉ ዘር ፍሬ ማኩረት የሚችል ፈሳሽ አዳብረዋል።እንደተመራማሪዎቹ ግምት ግንታቸዉ ከአምስት እስከ ሰባት አመት ባለዉ ጊዜ ለአገልግሎት ይዉላል።አንዳድ የመስኩ ባለሙያዎች ግን አዲሱን ግኝት ያልተሟላ በማለት አልተቀበሉትም። ሐና ደምሴ ከለንደን ዝር ዝር ዘገባ ልካልናለች።
ነጋሽ መሐመድ/ሸዋዬ ለገሠ